ድርጅታችን አለማየሁ ከተማ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ የእውቅና ሽልማት ተበረከተለት።

ድርጅታችን አለማየሁ ከተማ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ የእውቅና ሽልማት ተበረከተለት።

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የሰጠን የእውቅና ሽልማት ድርጅታችን እያስገነባው ባለው የማህበረሰብ ተጠቃሚ ፕሮጀክቶች ነው። ፕሮጀክቶቹ በባሌ ሮቤ ከተማ “ዘበላ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት” እና በባሌ ዞን በሃረና ቡሉቅ ወረዳ “የሻዌ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት” ልማት ግንባታዎች ናቸው። የዘበላ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት 7 ብሎክ እና 21 ክፍሎች ሲኖሩት የቤተ መፅሐፍት እና የቤተ ሙከራ ክፍሎችንም ያካተተ ነው። ለግንባታውም 15 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገ ሲሆን የ“የሻዌ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በበኩሉ 3 ብሎክ እና 12 ክፍሎችን ያካትታል። ለግንባታውም 12 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደረጓል። ት/ቤቶቹ የአካባቢውን ነዋሪዎች ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ድርጅታችን አለማየሁ ከተማ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ሌሎች የልማት ስራዎችን ለህብረተሰቡ ሰርቶ ለማስረከብ ጠንክሮ እንድሚሰራ እንገልፃለን።

 

Related posts

Leave your comment Required fields are marked *