ባለ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታው የባሌ ሮቤ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ግንባታ ፕሮጀክት
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ ግብርና መር ለሆነው ለሀገራችን ኢኮኖሚ ያለው ጠቀሜታ ዘርፈ ብዙ ነው። መንግስትም ለዘርፉ ልዩ የሆነ ትኩረት በመስጠትና ከፍተኛ የሆነ በጀት በመመደብ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በማስገንባት ላይ ይገኛል።
ከነዚህም ዘርፈ ብዙ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የሆነው የባሌ ሮቤ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ግንባታ ፕሮጀክት /Bale Robe Rural Transformations Centre Project/ በድርጅታችን አለማየሁ ከተማ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ አጥጋቢ በሚባል ሁኔታ በመገንባት ላይ ይገኛል። ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በአካባቢው የሚገኘውን ከፍተኛ የሆነ የእህል አቅርቦት እና የእንስሳት ተዋጽዎ ለማቀነባበር የሚረዳ ሲሆን ለአካባቢው ነዋሪዎችም ከፍተኛ የስራ ዕድልን የሚፈጥር ነው። ድርጅታችንም የፕሮጀክቱን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ በመረዳት ሥራውን በጥራት በመስራት በተቀመጠለት የጊዜ ሠሌዳ አጠናቆ ለመንግስት ለማስረከብ ቀን ከሌሊት በታላቅ ትጋት በመስራት ላይ ይገኛል። ከዚህ በተጨማሪም በአካባቢው የሚገኘውን ማህበረሰብ የኑሮ ሁኔታ በተጨባጭ ለማሻሻል የሚረዱ መልካም ተግባራት ላይ በመሰማራትም ላይ ነው። የዘይበላ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶት እድሳት እና የ ጤና ተቋም ግንባታ ለዚህ ዓይነተኛ ምሳሌዎች ናቸው።